ኬኒያ

#Kenya










ጎረቤት ኬንያ ታቃውሞ እየናጣት ነው።

መንግሥት በታክስ ላይ ጭማሪ ሊያደርግ ማቀዱን ተከትሎ በተለይም ወጣቱ ለተቃውሞ አደባባይ ወጥቷል።

ከወጣቶቹ ሰልፍ ጋራ በተያያዘ ትላንት አንድ ሰው #ተገድሏል፡፡

ግድያው የተፈጸመው በፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ነው ተብሏል።

ዛሬም በናይሮቢና የተለያዩ ከተሞች ተቃውሞ ሲካሄድ ውሏል። 

ተቃዋሚዎቹ በሚቀጥለው ሳምንት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሔድ የተቃውሞ ሰልፍ መጥራታቸው ተነግሯል።

ይህ በኬንያ ወጣቶች መሪነት የተነሳው እና ባለፈው ማክሰኞ በናይሮቢ ከተማ ተጀምሮ በመላው አገሪቱ የተሰራጨው ተቃውሞ በመጭው ማክሰኞ ብሔራዊ የሥራ ማቆም አድማ እንዲደረግ ጥሪ ማቅረቡ ተሰምቷል።

ተቃዋሚዎቹ ለምን አደባባይ ወጡ ?

ተቃዋሚዎች በሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ደስተኛ አይደሉም። 

አካሄዳቸውም ለብዙ ኬንያውያን ኑሯቸውን አስቸጋሪ ማድረጉን ይገልጻሉ።

በተለይም መንግሥት አሁን ያዘጋጀው የታክስ ጭማሪ ረቂቅ አዋጅ የህዝቡን ኑሮ የሚያመሰቃቅል እንደሆነ በመግለጽ እየተቃወሙ ነው።

የታክስ ጭማሪውን በመቃወም ለወራት በማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ሲደረግ ቆይቶ ነው ወደ ተቃውሞ ሰልፍ የተቀየረው።

የኬንያ መንግሥት ምን ይላል ?

መንግሥት የታክስ ጭማሪ ሊያደርግ ያቀደው ብድር ለመክፈል እና ለልማት ሥራዎች እንደሆነ ገልጿል።

ተቃውሞውን ተከትሎ ከረቂቅ አዋጁ ላይ የተወሰኑትን እንደሚተው ቢያስታውቅም ተቃውሞው ግን ዛሬም ቀጥሏል።

የታክስ ጭማሪው ምን ላይ ነው ?

መንግሥት በያዘው እቅድ የታክስ ጭማሪው በተለያዩ ሸቀጦች ላይ የሚደረግ ነው።

በነዳጅ ላይ ሊጨመር የታሰበው 9 ሺልንግ ሲሆን ጭማሪው ለፈረሱ መንገዶች መጠገኛ እንደሚሆን የአዋጁ አርቃቂዎች አስታውቀዋል።

መንግስት በተጨማሪ አካባቢን ለመጠበቅ በሚል ታክስ ለመጣል ያቀደ ሲሆን ይህም ደግሞ የፕላስቲ ውጤቶች የሚያስከትሉትን ብከላ ለመከላከል እንደሆነ አስታውቋል።

ብሔራዊ ሸንጎው ረቂቅ አዋጁን ሚቀጥለው ሳምንት እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል። 

ለተቃውሞ የወጡት ኬንያውያን ግን በተቃውሟቸው እንደሚገፉበት አስታውቀዋል።

#AFP
#VOA
#Kenya 



አስተያየት ይለጥፉ

አዲስ የድሮ

Blog ads

Betseb media