አዲስ አበባ እና ውሃ ?
" ኧረ የመፍትሄ ያለህ " - ነዋሪዎች
" ችግሩ የውሃ አቅርቦት አይደለም። የኤሌክትሪክ ኃይል ስለሚቋረጥ ነው " - የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን
" ለ15 ቀን እና ከአንድ ወር በላይ ውሃ እንዲጠፋ የሚያደርግ የኃይል መቋረጥ ገጥሞ አያውቅም " - የኤሌክትሪክ አገልግሎት
በሀገሪቱ ዋና ከተማ በአዲስ አበባ የሚኖሩ ነዋሪዎች ውሃ በፍረቃ ያውም በሳምንት ሁለት ቀን ብቻ እያገኙ አመታት አልፈዋል።
በሳምንት ሁለት ቀን የማይመጣበትም አለ።
ዛሬም ድረስ በመዲናው ያለው የውሃ ችግር (በተለይም በአንዳንድ ቦታዎች ላይ) ከመፈታት ይልቅ እየባሰበት ነው እየሄደ ያለው።
ውሃ በፈረቃ ቢመጣም ኃይል ስለሌለው በተለይ ፎቅ ላይ የሚኖሩ ዜጎች ውሃ አያገኙም። አንዳንድ ጊዜ በፈረቃ ጭራሽ ላይመጣም ይችላል።
ይህ የአያት 49 ቁጥር 2 አካባቢ ነዋሪዎች እያሳለፉ ስላሉት የከፋ ችግር ለኤፍቢሲ የሰጡት ቃል ነው ፦
ነዋሪ 1.
" ላለፉት 8 ዓመት እዚህ ነው ያለሁት። የመጀመሪያ ፎቅ ላይ ነው ያሉት የውሃ ችግር በጣም burning ነው። እንኳን ኮንዶሚኒየም ቀርቶ ቪላ ቤት ውስጥ ውሃ ያስፈልጋል። እሮብ እና ሀሙስ ነው ቀናችን እሮብ ሙሉ ቀን አይመጣም። ለምሳሌ ፥ ሀሙስ 8 ሰዓት መጣ 11 ሰዓት ተዘጋ፤ ኡኡ ስንል የቴክኒካል ቃላትን ይጠቀማሉ ሰዎቹ ፤ በስርጭታችን መሰረት ማግኘት እንፈልጋለን። "
ነዋሪ 2.
" እኛ 50 ብር ለውሃው እንቀዳለን። ወደላይ ማስወጫ ለአንድ ጄሪካን 20 ብር እንከፍላለን። 4ኛ ላይ ስለሆንኩኝ ወደላይ ፓወር ስለሌለው ስለማይወጣ ለአንድ ጄሪካን 70 ብር እየከፈልን ነው የምንቀዳው። "
ነዋሪ 3.
" ታች ግራውንድ አለ ፎቅ ላይ አንድም ውሃ የለም። ይኸው ወራችን ነው። "
ነዋሪ 4.
" እኛ እዚህ ሰፈር ከገባን አስር (10) ዓመታችን ነው። የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ነን። ከ10 ዓመታ ይሄ 3 ዓመት የምንገባበት ቀዳዳ አጥተናል። በአሁኑ እንኳን ውሃ ሳላገኝ 1 ወሬ ነው። 1 ወር ሙሉ ውሃ ማጣት ማለት ምን ማለት ነው ? "
ነዋሪዎች መፍትሄ ይሰጠን ይላሉ።
ውሃና ፍሳሽ ሲጠይቁ " መብራት የለም " የሚል ነው መልሱ።
የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ለኤፍቢሲ በሰጠው ቃል ፥ " ውሃ እየሰጠን እየሄደ እያለ በተደጋጋሚ መብራት ይጠፋል። ለምሳሌ 3ኛ ላይ ውሃው ደርሶ እያለ መብራት ከጠፋ ውሃው ወደኃላ ይመለሳል " ብሏል።
መስሪያ ቤቱ ፥ " የውሃ አቅርቦት ችግር የለም። ችግሩ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ነው። ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር እየሰራን ነው። እያንዳንዱ መብራት ሲጠፋ ሪፖርት የማድረግ ፣ የመናበብ ስራ አለ " ሲል ገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ፤ " የውሃ ስርጭት እንዲቋረጥ የሚያደርግ የከፋ የኃይል መቋረጥ ገጥሞ አያውቅም ፤ በተቋም ደረጃ ቅሬታ ቀርቦም አያቅም። 1 ወር እና 15 ቀን በላይ ውሃ ጠፍቶ ምክንያቱ ኤሌክትሪክ ኃይል ነው የሚል ነገር መረጃ ጭራሽ ደርሶን አያውቅም። " ሲል መልሷል።