በፍሎሪዳ

በፍሎሪዳ አንዲት የማክዶናልድ ሰራተኛ በምግብ ትዕዛዝ ላይ በተፈጠረ አለመግባባት ደንበኛን ላይ ተኩስ በመክፈቷ በቁጥጥር ስር ዋለች

የፍሎሪዳ ማክዶናልድ ሰራተኛ ባለፈው ሳምንት በአሽከርካሪዎች መስኮት ላይ በተፈጠረ አለመግባባት ደንበኛን በጥይት ለመምታት ተኩስ መክፈቷን ፖሊስ አስታዉቋል።

የ22 አመቷ ቻሲዲ ጋርድነር የሌክላንድ ነዋሪ ስትሆን አርብ እለት ከተፈጠረዉ ክስተት ጋር በተያያዘ በከባድ መሳሪያ ጥቃት ተከሳለች።የሌክላንድ ፖሊስ መኮንኖች እንዳስታወቁት አርብ ከጠዋቱ 1 ሰአት አካባቢ በፈጣን ምግብ ሬስቶራንት ላይ ተኩስ የነበረ ሲሆን በጋርነር እና በመኪና የመጣ አሽከርካሪ በመስኮቱ በኩል ባዘዘዉ ምግብ ላይ ቅሬታ በማሰማት በደንበኛ መካከል በተነሳ ክርክር ጉዳዩ አጋጥሟል፡፡

በክርክሩ ወቅት ጋርድነር ደንበኛዉ ላይ መጠጥ እንደወረወረች ፖሊስ አስታዉቋል።ደንበኛዉ በተራዉ በመስኮቱ በኩል ክንዱን አዉጥቶ አንዳንድ እቃዎችን ወለሉ ላይ ሲጥል ተስተዉሏል። ከደንበኞቹ ሁለቱ ከተሽከርካሪዉ ሲወርዱ ጋርድነር የሽጉጥ ጥቃት ከፍታለች፡፡ ተሽከርካሪው ከፓርኪንግ ቦታው ላይ ሲወጣ ተኩስ እንደከፈተች ተነግሯል።መኪናው ቢያንስ አንድ ጊዜ ተመቷል። በሰዉ ላይ ግን ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም።

አስተያየት ይለጥፉ

አዲስ የድሮ

Blog ads

Betseb media