ከፍታ





ከፍታ የአዳማ ወጣቶች ገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/መሰረታዊ የህብረት ሥራ ማህበር
ከፍታ የአዳማ ወጣቶች ገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተወ/መሰረታዊ የህብረት ሥራ ማህበር የወጣቶች አንዱና ዋነኛ የሆነዉን የፋይናንስ ወይም የብድር አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ ከ አዳማ ከተማ የህብረት ሥራ ማደራጃ ጽ/ቤት የሥራ ፈቃድ አግኝቶ እጣ ወይም አክሲዮን በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡ የህብረት ሥራ ማህበሩ ወጣቶች የሚመሩት ፤ ወጣቶች ባለቤት የሆኑበትና የሚያስተዳድሩት ማህበር ነዉ፡፡
የማህበሩ ዓላማ
  ለወጣቶች ምቹ እና ተደራሽ የሆኑ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር አገልግሎቶችን በማቅረብ የወጣቶችን  ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኑሮ ማሻሻል 
  ወጣቶች ከህብረት ሥራ ማህበሩ በአነስተኛ ወለድ የሚያገኙትን ብድር  አዋጭ በሆኑ የሥራ ዘርፎች ላይ በማዋል ለራሳቸዉ እና ለሌሎች የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩ ድጋፍ እና ክትትል ማድረግ 
  የተለያዩ ሥልጠናዎችንና ትምህርቶችን በማዘጋጀት የማህበሩ አባላት ገንዘባቸዉን በአግባቡ እና በተገቢ መንገድ እንዲጠቀሙ በማድረግ የገንዘብ ቁጠባ ባህላቸዉ እንዲጎልበት ማድረግ
ህብረት ሥራ ማህበሩ የሚሰጣቸዉ አገልግሎቶች
  የመደበኛ ቁጠባ ፤ የፈቃደኝነት ቁጠባ ፤የትምህርት ቁጠባ ፤ የህጻናት ቁጠባና የ አዋቂዎች ቁጠባ
  ለንግድ ሥራ መጀመርያ እና ማስፋፍያ ፤ ለትምህርት እና ለሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች የሚሆን ብድር
ከሌሎች የገንዘብ ቁጠባና ብድር የሚለዩን አገልግሎቶች
  ቁጠባ በጀመሩ ከ 4 እስከ 6 ወር  ዉስጥ የተለያዩ የብድር አገልግሎቶችን በአነስተኛ ወለድ  እናበድራለን 
  የቆጠቡትን የገንዘብ መጠን እስከ አራት እጥፍ መበደር ይችላሉ
  ለወጣቱ ምቹ የሆኑ የተለያዩ የብድር ዋስትና አማራጮች አሉን
  የንግድ ሥራ ሥልጠና እና የምክር አገልግሎት በነጻ እንሰጣለን
አባል ለመሆን የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
  ዕድሜ ከ 18 እስከ 29 ዓመት የሆነዉ/የሆናት እና ሙሉ ፍላጎት ያላዉ/ያላት
  ዝቅተኛ የዕጣ መጠን ማለትም 4 ዕጣዎችን በ 1000 ብር መግዛት የሚችል/የምትችል፡፡ የ 1 ዕጣ ዋጋ 250 ብር ነው
  በየወሩ መደበኛ የሆነ 300 ብር መቆጣብ የሚችል/የምትችል
  የመመዝገቢያ 200 ብር መክፈል የሚችል/የምትችል
  የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ/ መንጃ ፈቃድ/ ፓስፖርት ያለዉ/ያላት
የህብረት ሥራ ማህበር አባል ለመሆን ከወሰኑ 1200 ብር (የ 4 ዕጣ ዋጋና የመመዝገብያ ክፍያ)
በ አዋሽ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 01303959826900 ላይ በማስገባት ፈጥነዉ ይቀላቀሉን !
የከፈሉበትን ደረሰኝ ይዞ ሲመጡ የማህበሩ ደረሰኝ ይሰጦታል !
አድራሻችን ፡  ወደ ፒኮክ በሚወስደዉ መንገድ 50 ሜትር ገባ ብሎ YNSD ቢሮ ያለበት ጊቢ ዉስጥ እንገኛለን፡፡
ስልክ ቁጥር   0912131689/....
ኑ! አብረን ከፍ እንበል !!
ከፍታ የወጣቱ አለኝታ 

አስተያየት ይለጥፉ

አዲስ የድሮ

Blog ads

Betseb media