አሜሪካን



ትራምፕ በአሜሪካ ኮሌጆች ተምረው ሊሚመረቁ የውጭ ሀገራት ተማሪዎች ግሪን ካርድ እሰጣለሁ አሉ

በኢሚግሬሽን ላይ ባላቸው ጠንካራ አቋም የሚታወቁት የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ ተምረው የሚመረቁ ሰዎች በአገር ውስጥ መቆየት መቻል አለባቸው ብለዋል።

የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በ2024ቱ ምርጫ ከተመረጡ በአሜሪካ ኮሌጆች ለሚገኙ የውጭ ሀገራት ምሩቃን ግሪን ካርድን እንደሚሰጡ የገለፁ ሲሆን ይሄም በኢምግሬሽንና ስደተኞች ላይ የነበራቸውን ጠንካራ አቋም መለሳለሱ ማሳያ ተብሏል።

ሐሙስ ዕለት ከሲሊኮን ቫሊ የቴክኖሎጂ ባለሀብቶች ጋር በፖድካስት ቃለ መጠይቅ ላይ ትራምፕ ተሰጥኦዎችን ወደ አሜሪካ ለማምጣት ቀላል ለማድረግ ቃል በመግባት ማንኛውም ከአሜሪካ ኮሌጅ የሚመረቅ ሰው በአገሪቷ መቆየት መቻል አለበት ብለዋል።

ትራምፕ ኦል-ኢን ፖድካስት ላይ “ከሃርቫርድ፣ MITና ሌሎች ታላላቅ ትምህርት ቤቶች ያፈሩዋቸውን ሰዎችን ስናጣ በጣም ያሳዝናል ብለዋል። ትራምፕ አክለውም “በዚህ አገር ለመቆየት እንድትችል እንደ ዲፕሎማህ አካል ግሪን ካርድ ወዲያውኑ ማግኘት ያለብህ ይመስለኛል” ሲሉ ትራምፕ ገልፀዋል።

ግሪን ካርድ ለግለሰቦች በአሜሪካ ውስጥ በቋሚነት የመኖር እና የመስራት መብትን እንዲሁም የሀገሪቱን የዜግነት ማግኛ መንገድን ያመቻቻል። በየዓመቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አዲስ የዜግነት አመልካቾችን ይፈጥራል የተባለው የትራምፕ ሀሳብ በሪፐብሊካን ፓርቲ ውስጥ ከፍተኛ ተቀባይነትና ቦታ እንዲያገኝ ካደረገው የኢሚግሬሽን ጠንካራ አቋም መውጣቱን ያሳያልም ተብሎለታል።

በአንድ ወቅት ስደተኞች “የአገራችንን ደም እየበከሉ ነው” ያሉት ትራምፕ በአሜሪካ ታሪክ ትልቁ የሆነውን ሰነድ አልባ ስደተኞችን ለማባረር ቃል ገብተውም ነበር።

ማክሰኞ በዊስኮንሲን ውስጥ በተካሄደው የዘመቻ ዝግጅት ላይ ትራምፕ በዚህ ሳምንት ባወጁት ፕሮግራም ላይ ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው የአሜሪካ ነዋሪዎች ባለትዳሮች ጨመ ከአገሪቱ መውጣት ሳያስፈልጋቸው ለቋሚ መኖሪያነት እንዲያመለክቱ ያስችላቸዋል። “አገራችን በወረራ ላይ ነች። አሁን ስለ ሌላ ነገር መነጋገር የለብንም ፣ ይልቁንም ወረራውን ለማስቆም መነጋገር አለብን ብለዋል።

የአገር ውስጥ ደህንነት ዲፓርትመንት ባወጣው ግምታዊ ቁጥር መሠረት 11 ሚሊዮን የሚሆኑ ስደተኞች ያለፈቃድ በአሜሪካ ይኖራሉ ብሎል። ትራምፕ በኦል-ኢን Podcast ላይ በታዩበት ወቅት ምንም እንኳን በቀደመው የስልጣን ዘመናቸው ግሪን ካርዶችን ለተመራቂ ተማሪዎች የመስጠት እቅድ የነበራቸው እንደሆነ ቢገልፅም የኮቪድ ወረርሽኙ ግን ግሪን ካርዶችን ለውጭ ተመራቂዎች የመስጠት እቅዱን እንዳስተጓጎለው ገልፀዋል።


አስተያየት ይለጥፉ

አዲስ የድሮ

Blog ads

Betseb media