በተራራማ ስፍራ ለቀናት ጠፍቶ የነበረው ሰው በቀን 4 ሊትር ውኃ እየጠጣ ሕይወቱን ማቆየቱ ተሰማ

በተራራማ ስፍራ ለቀናት ጠፍቶ የነበረው ሰው በቀን 4 ሊትር ውኃ እየጠጣ ሕይወቱን ማቆየቱ ተሰማ
**********************







በአሜሪካዋ ካሊፎርኒያ ግዛት ለእግር ጉዞ ወጥቶ ለ10 ቀናት በተራራማ ስፍራ ጠፍቶ የነበረው ግለሰብ በቀን እስከ 4 ሊትር ውኃ እየጠጣ ሕይወቱን ማቆየቱ ተሰምቷል።

ሉካስ ማክሊሽ የተባለው ይህ የ34 ዓመት ግለሰብ በካሊፎርኒያ ሳንታ ክሩዝ ተራራማ ቦታ ለሦስት ሰዓታት የእግር ጉዞ ለማድረግ ከወጣ በኋላ ነበር ጠፍቶ የቆየው።

ማክሊሽ ተራራ በመውጣት ልምድ ያለው ቢሆንም በቅርቡ በተራራማ አካባቢው የተነሳው እሳት አቅጣጫ ጠቋሚዎችን በማውደሙ መመለሻው ጠፍቶበት 10 ቀናትን በጫካ ውስጥ ለመቆየት መገደዱ ተጠቅሷል። 

በተራራው ስፍራ የእግር ጉዞ ለማድረግ ወጥቶ ሳይመለስ ሲቀር የቤተሰብ አባላት ለፖሊስ ጥቆማ ሰጥተው ለቀናት የቆየ ፍለጋ ሲደረግ መቆየቱም ነው የተገለፀው።

ፖሊስ ማክሊሽን ለማግኘት ሲያደርግ የነበረው ጥረት ተሳክቶ በአሳሽ ድሮን (ሰው አልባ አውሮፕን) እግዛ ግለሰቡ በህይወት ሊገኝ መቻሉ ተጠቁሟል።

ፖሊስ በርካታ ሰዎች የማክሊሽን የድረሱልኝ ጩኸት ቢሰሙም ማክሊሽ ያለበትን ቦታ መለየት አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል ብሏል።

ሉካስ ማክሊሽ በአሳሽ ድሮን እገዛ ከ10 ቀናት በኋላ በህይወት እንደተገኘ ለጋዜጠኖች በሰጠው ቃል፤ በጫማው አማካይነት ውሃ እየሰበሰበ ሲጠጣ እንደነበረ ገልጿል።

“በየቀኑ እስከ 4 ሊትር ውሃ መጠጣቴን እርግጠኛ መሆን ነበረብኝ” ያለው ማክሊሽ፤ የዱር ፍሬዎችን እየለቀመ መብላቱንም ጨምሮ ተናግሯል።

ፖሊስ በርካታ አባላቱን በማሰማራት ለፍለጋ ወጥተው በሕይወት ስለደረሱለት ማክሊሽ ምስጋናውን ማቅረቡን ኤቢሲ ኒውስ ዘግቧል።

አስተያየት ይለጥፉ

አዲስ የድሮ

Blog ads

Betseb media