በጎፋ ዞን







በጎፋ ዞን በደረሰ የመሬት ናዳ የሟቾች ቁጥር ከ229 በላይ መድረሱ ተነገረ‼️

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበል በትላንትናው እለት ሀምሌ 15 ከረፋዱ 4:00 ሰዓት አካባቢ በደረሰ የመሬት ናዳ የሟቾች ቁጥር ከ229 በላይ መድረሱ ተገልጿል፡፡

በቀበሌው ናዳው ከደረሰ በኋላ የሠው ህይወት ለመታደግ ወደ በስፍራው ለነፍስ አድን ተግባር የተሰበሰቡ የአካባቢው ነዋሪዎች የአደጋው ሰለባ መሆናቸውን  የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ኢንስፔክተር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።በትላንትናው እለት የወረዳው ፖሊስ አዛዥ የተለያዩ የፖሊስ አባላትን ይዘው ወደ ቦታው ሲያመሩ ተንሸራተው የነበረ ሲሆን በገመድ ተጓትተው  በህይወት መትረፍ መቻላቸውን ለጣቢያችን ተነግረዋል።

ከተለያዩ አካባቢዎች ለእርዳታ የመጡ ነዋሪዎች በቀበሌው በርካቶች በመሆናቸው የነዋሪዎች ቁጥር በውል እንደማይታወቅ ነው የተነገረው፤ በአደጋው ሰለባ ከሆኑት ሰዎች መካከል የወረዳው ፖሊስ አባላትን ጨምሮ ሴቶችና ሕፃናት የሚገኙ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የአስክሬን ፍለጋና የነፍስ አድን ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልፆል፡፡
ለአደጋ ተጋጭ ናቸው ተብለው የተለዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ወደ ተለያዩ ትምህርት ቤቶች እና ቀበሌዎች የማጓጓዝ ስራ እየተሰራ ነው፡፡የአስከሬን ፍለጋ ስራው ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው የተባለ ሲሆን በቀጣይ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል  ኢንስፔክተር አሸናፊ ኃይሌ ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

በተከናወነዉ የነፍስ አድን ስራ ከናዳ ውስጥ አምስት ሰዎች በህይወት የተገኙ ሲሆን ከዚህ በኋላ በህይወት የሚገኙ ሰዎች ላይኖሩ ይችላል የሚል ግምት ተሰጥቷል።ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ሰዓት ድረስ የሟቾች ቁጥር 229 መሆኑን ብስራት ሰምቷል፡፡ከአደጋዉ በህይወት የተረፉ ሰዎች ቤት ንብረታቸዉ በመዉደሙ የተነሳ አስቸኳይ የረድኤት ድጋፍ ሊደረግላቸዉ እንደሚገባ ጥሪ በመቅረብ ላይ ይገኛል፡:


አስተያየት ይለጥፉ

አዲስ የድሮ

Blog ads

Betseb media