አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2016 የተማሪ ቅበላ በነባሩ ስርዓት እንደሚቀጥል ገለጸ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2016 የተማሪ ቅበላ በነባሩ ስርዓት የሚቀጥል መሆኑንና አዲስ አሰራሮች ከመጡ በየጊዜው እንደሚያሳውቅ የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ገለጹ።
ዶክተር ሳሙኤል በዩኒቨርሲቲው እየተከናወኑ ያሉ የሪፎርም ስራዎችን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሀን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
በዚህም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝነት ታውጆ ወደ ስራ መገባቱንና፤ የሽግግሩን ሂደት የሚመሩ አመራሮች መመደባቸውንም ገልጸዋል።
አዲሱ አመራር ከመስከረም ሁለት ጀምሮ ወደ ስራ መግባቱን የገለጹት ዶክተር ሳሙኤል፤ በተደረጉ ጉብኝቶችና ውይይቶችም ብዙ ጉድለቶችን መመልከት መቻሉን አስረድተዋል።
በውይይቶቹም በአግባቡ ለመስራት ከስምምነት ላይ መደረሱን እና የሽግግር ሂደቱ የሚመራበት እቅድ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።
የሽግግር ሂደቱ እስኪጠናቀቅ ድረስም ነባር አሰራሮች ባሉበት እየቀጠሉ የሚተኩ አሰራሮችን በየጊዜው የማሳወቅ ስራዎች ይሰራሉ ብለዋል።
በጊዜያዊነት የሽግግር ሂደቱን የሚመሩ አመራሮች ስራቸውን እንዳጠናቀቁ በዓለም አቀፍ መስፈርቶች ለሚመረጠው አመራር ኃላፊነታቸውን ያስረክባሉ ማለታቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።
የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ‼️
የዓለም ቅርስ ኮሚቴ በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ውሳኔ አሳልፏል።
የባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ በቅርስነት የተመዘገበው በኢትዮጰያ ሁለተኛው ታላቅ የተፈጥሮ ቅርስ ሆኖ ሲሆን በዓለም ደግሞ 11ኛው ቅርስ በመሆን ነው።
45ኛው የአለም የቅርስ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ሁለት ታላለቅ የቱሪስት መዳረሻዎችን በአለም ቅርስነት ማስመዝገቧን የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡
×