MrJazsohanisharma

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ

ከተቀመጠው አሰራር ውጪ የመኖሪያ ቤት ዋጋ ጭማሪ ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ ነው

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ




 
የአከራይ ተከራይ አዋጅ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በህግ ከተቀመጠው አሰራር ውጪ የመኖሪያ ቤት ዋጋ ጭማሪ ማድረግና የነበረውን የኪራይ ውል ማቋረጥ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል፡፡
 
በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ፍትሀዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በማህበረሰቡ ላይ የሚፈጥረው ጫና ከግምት ውስጥ በማስገባት የቤት ኪራይ ስርአቱ በህግ የሚመራ እና ተገቢውን ቁጥጥር በማድረግ ለችግሩ አፋጣኝ ምላሽ መስጠት ተገቢ ሆኖ ሰለታመነበት የመኖሪያ ቤት ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 መጋቢት 24/2016 መውጣቱ ይታወቃል።
 
የከተማ አስተዳደሩም የአዋጁን ማስፈፀሚያ መመሪያ ቁጥር 7/2016 በማውጣት ተግባራዊ አድርጓል።በመሆኑም አዋጁ ወጥቶ ተግባራዊ ከሆነበት ቀን ማለትም ከመጋቢት 24/2016 ጀምሮ መንግስት ከሚያስቀምጠው የኪራይ ውሳኔ ውጪ በአከራዮች የሚደረግ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ፈፅሞ የተከለከለ በመሆኑ አዋጁ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከህግ ከተቀመጠው አሰራር ውጪ የመኖሪያ ቤት ዋጋ ጭማሪ ማድረግና የነበረውን የኪራይ ውል ማቋረጥ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ቢሮው ገልጿል።
 
ይህ እንዳይፈፀምም ቢሮው ተገቢውን ቁጥጥር እና ክትትል እንደሚያደርግም ማስታወቁን ከአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡የህግ ክልከላውን ተላልፈው የተገኙ አከራዮች ላይ በመመሪያ ቁጥር 7/2016 አንቀፅ 22 መሰረት አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድም ቢሮው አሳስቧል።

አስተያየት ይለጥፉ

አዲስ የድሮ

Blog ads

Betseb media